Friday, April 12, 2013

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ፤ በራያ ዓዘቦ ወረዳ መንግስት ህገ ወጥ ናቸው በሚል ሰበብ መኖርያ ቤቶችን ማፍረስ ጀምረ፣



መንግስት የጸጥታ ሃይሎችን በማሰማራትና አከባቢውን በመክበብ ኗሪው ለብዙ ዓመታት የኖረባቸውን መኖሪያ ቤቶችን እንዲፈርሱ በማስገደድ ከ 1300 መኖሪያ ቤቶች በላይ በማፍረሱ እድሚያቸው የገፉ ወላጆች ፤ ሴቶችና ህጻናት ያለመጠልያ ባዶ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ፣
የተጀመረው ቤት የማፍረሱ ተግባር የሚቀጥል ሲሆን ገና ተጨማሪ 600 መኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ መንግስት መወሰኑን ቷውቋል፣
ኗሪዎቹ በጸጥታ ሃይሎች ጫና ቤታቸውን እንዲያፈርሱ በተደረገበት ወቅት አንድ የአከባቢው ኗሪ ቤቱ በማፍረስ ላይ እያለ ተደርምሶበት ህይወቱን አጥቷል፣
መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው የአከባቢው ኗሪዎች ከመካከላቸው የተወሰኑ ሰዎችን በመወከል ጉዳያቸውን ወደ ክልልና ፌደራል መንግስት በማቅረብ መፍትሄ በመፈለግ ላይ መሆናቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣