Wednesday, January 1, 2014

ፀረ-ህዝብ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት የህዝብ ሃብት እየሰረቁ ለግልና ለቤተሰባቸው ኑሮ እያዋሉት እንደሆኑ ከተለያየ የሃገራችን አካባቢ የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣




      በመረጃው መሰረት ህዝባዊና ሃገራዊ ራኢ የሌላቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት በንፁሃን የህዝብ ልጆች ስንክልናና መስዋእት ስልጣን ከተቆጣጠሩ በ23 አመታት ውስጥ፤ የስርዓት ለውጥ በማድረግ ማህበራዊና ቁጠባዊ እድገት በሃገር ለማየት ተስፋ አድርጎ ለነበረው መላዉ የሃገራችን ህዝብ ወደጎን ረስተው፤ የኣገሪቱ ሃብት በሚያገኙት አጋጣሚ እየሰረቁ ካዘናቸዉ እየሞሉና ከዚህም ባሻገር በልጆቻቸውና በቤሰሰቦቻቸው ስም በውጭም ሆነ ባገር ውስጥ  ትላልቅ ተቋማት እየሰሩ ኑሮአቸውን ሲያመቻቹ፤ ለጭቁኑ ህዝብ ግን ቀናብሎ የሚያዬው አካል አጥቶ በድህነትና በኋላ ቀርነት ተዘፍቆ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችልዋል፣
    በዚህ መጥፎ በሆነ አካሄዳቸው፤ በአሁኑ ግዜ የጠቅላይ ሚንስተር አማካሪ ሁኖ ተሹሞ ያለዉ በረከት ስምኦን በጎንደር ከተማ 01 ቀበሌ በተለምዶ አጠራሩ ብለኮ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ፤ ላንድ ማርክ በሚል ስያሜ ሆቴል አሰርቶ ታህሳስ 28 እንደሚያስመርቅ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
     እራሱ በረከት ሰምኦንና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተጋባዥ ሆነው በሚገኙበት በዚሁ ሆቴል፤ የምርቃቱ ስነ ስርኣት እንዳይታወቅ ሲባል  በሆነውና የጣፋጭ ኬክ ቤት ባለቤት ልጅ ለሆነው የኢንጅነር ነጋ ነዉ ቢባልም፤ እዉነታው ግን የሆቴሉ ባለቤት እራሱ በረከት ስምኦን እንደሆነ የጎንደር ከተማ ህዝብ በሚገባ እንደሚያውቅ። ለጎንደር ከተማ ነዋሪዎች መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስገነዘበ፣