የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት ለሁሉም የሃገራችን
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የራሳቸው አባል እንዲሆኑና ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.ን ብቻ እንዲመርጡ ቅስቀሳ እያካሄዱ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው።
ተማሪዎች ግን በአንድ ሃገር አንድ ድርጅት ሁሉንም ዜጎች አባል ሁኑ ማለቱ አደጋ አለው ለውጥ ማምጣት አይችልም ይህ የፖለቲካ ችግር
ነው በማለት አካሄዱን እንደተቃወሙት ለማወቅ ተችሏል፣
መረጃው ጨምሮም። የስርዓቱ ካድሬዎች የተማሪዎችን ትኩረት ለመሳብ የምርጫ
ቅስቀሳ ከፖለቲካ ሳይንስ ጋር ለማያያዝ የሞከሩ ሲሆን። ተማሪዎች ግን
ይህ የማደናገር መላችሁ ጊዜው ያለፈበትና ለበርካታ መምህራን
የስራ ማቆም ምክንያት የሆነ ነው በማለት ስለተቃወሟቸው። መድረክ መሪ የነበሩትም ያሰቡት ስላልተሳካላቸው ስብሰባውን አቋርጠው እንደሄዱ
ሊታወቅ ተችሏል፣