Thursday, April 3, 2014

በአገር ደረጃ በመቐለና በባህርዳር፤ በአዲስ አበባ አዋሳና ደሬዳዋ ደግሞ በፕላዝማ ስክሪን የተሰጠ ስልጠና ላይ በአማራሮቹ በርካታ ጥያቄዎች እየስነሳ እንደሚገኝ ተገለፀ።



በከፍተኛ አመራር ደረጃ በአቶ አዲሱ ለገሰና ሌሎች ሁለት ሚንስተር ዲኤታዎች እየተመራ ለኢህአዴግ ስርአት አመራሮች በተሰጠ ስልጠና ላይ አምስት የተመረጡ መጽሓፎች ለ41 ቀናት የቀረቡ ሲሆኑ በመጀመርያ ደረጃ የዴሞክራሲ ግንባታ በኢትዮጵያ የሚልና  ፖሊሲና እስትራተጂ በኢትዮጵያ የሚል እንደሆነ ሊታወቅ ተችለዋል።
   በባህርዳር ከተማ ከሚገኙ 985 ሰልጣኞች ውስጥ ከተነሱ ጥያቄዎች
-    መሪዎቻችችን ለኛ ይህን ለህዝቡ አእምሮአችን በሚነካ መንገድ እየሰደቡን ነው፣ ለምን ለአማራ ትምክህተኛና ትእቤተኛ ነው ይሉታል?
-    የአገራችን መሬት ለምን ለሱዳን ተሽጠ? በምን ምክንያትስ ተሸጠ?
-    በግብር አሰባሰብ ዙርያ ፍትሃዉነት ስለሌለ ህብረተሰቡ በችግር ወድቀዋል ለምን አይታይም የሚሉና ሌሎች ጥያቂዎች እንደተነሱ ለማወቅ ተችለዋል፣
    ይህ በግብር አሰባሰብ ዙርያ የተነሳ ጥያቄ በሰብሳቢዎች ምላሽ የተሰጠው ቢሆንም ለቀረው ጥያቄ ከአቅማችን በላይ ነው በማለት አድበስብሰዉት እንዳለፉ ታውቋል።
     ይህ በፕላዝማ የተካየደው ስልጠና አዲስ ፈጠራ ስላለው ሳይሆን፤ ለህዝብ እና ለአገር እየበደሉና እየበዘበዙ የቁዩበት 23 አመት የስልጣን እድሜያቸው ለማራዘምና በኢትዮጵያ ህዝብ እያጋጠማቸው ያለው ተቃዉሞ ትልቅ ስጋት ሰለፈጠረባቸው መሆኑን የተለያዩ ወጎኖች እየገለፁ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድተዋ።