Tuesday, October 14, 2014

ከኢህአዴግ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በተለያዬ ምክንያት ተባረው የቆዩ መኮነኖች በምርጫው ሰዓት ህዝቡን ያነሳሳሉ በሚል ስጋት ስርዓቱ በጭንቀት ላይ ወድቆ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገለፁ፣



በጉጅሌው የኢህአዴግ ስርዓት በተከታታይ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ፤ እነዚህ የስርዓቱ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ምርጫውን በሚመለከት ያቀረቡት አጀንዳ፤ ምርጫ እየቀረበ ስለሆነ ለኢህአዴግ መንግስት እንዴት አድርገን እናግዝ የሚል ሓሳብ እንዳስነሱና፤ ከዚህ በፊት በተለያየ ምክንያት ከመከላከያ ሰራዊት ተባረው የነበሩ ከሻለቃ በላይ የሆኑ አመራሮች፤ በህዝብ ዘንድ ተሰሚነት ስላላቸው ብቻ ህዝቡን አደራጅተው ፀረ መንግስት እንዳይቀሳቀሱ በጥቅማ ጥቅም ማባበል ይገባናል በማለት እየተነጋገሩበት እንደሚገኙ ሊታወቅ ተችሏል፣
   ያገኘነው መረጃ እንደሚያመልክተው ጉጅሌው የኢህአዴግ መንግስት ከዚህ በፊት አታስፈልጉኝም ብሎ አባሯቸው የነበሩትን ወታደራዊ መኮነኖች ከያሉበት ቦታ እየሰበሰበ ታግላችኋል መንግስታችን እንድትጠቀሙ ይፈልጋችኋል እያለ በመስበክ ወደ ሰላም አስከባሪ እንስደዳችሁ የሚል ሃሳብም እንዳቀረበላቸው መረጃው ገልፆ። ይህ ደግሞ ጉጅሌው ባለስልጣናት እድሜ ለማራዘም የፈጠሩት ተንኮል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፣