በኢህአደግ ከፍተኛ አመራሮች መሪነት የገዢውን ጉጅሌ ስብሰባ ለሁሉም ካድሬዎችና አባላት እየተሰጠ እንዳለ የገለጸው መረጃው፤ የስብሰባው አጀንዳም በመጪው 2007
ዓ/ም ምርጫ ላይ እንዴት እየሄድን ነው፤ ምርጫን የሚመለከት የቀረን
ምን አለ፤ የምናደርገው ቅድመ ዝግጅት ካለስ ምን ማድረግ አለብን የሚሉና፤ እንዲሁም ሁሉም የታችኞቹ ካድሬዎቻችን ህዝቡ ለኢህአደግ
እንዲመርጥ አበርትተው መስራት አለባቸው በማለት፤ ጥብቅ መምርያ እንዳወረዱላቸው ታውቋል፣
እንደ ምንጮቻችን መረጃ ተሰብሳቢዎቹ
በኩላቸው ህዝቡ አጋጥሞት ካለው ከባድ የኑሮ ችግር ሳይፈታለት ስለ ምርጫ አመልክተን ብንናገር አይቀብለንም። ሰለዚህ ራሱ መንግስት
የህዝቡን የኑሮ ችግር መፈታት አለበት ሲሉ ያቀረቡትን ሃሳብ፤ የኢህአደግ ከፍተኛ አመራሮች ግን ሃሳቡን ስላልተቀበሉት ሳይስማሙ
ከስብሰባው እንደተበተኑ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣