የኢዮጵያ ህዝብ ባሁኑ
ግዜ እንደ ዘይት፤ ስኳር፤ የፊኖ ዱቄትና ተዛማጅ ነገሮችን በማጣቱና
ከገበያ ጠቅልለው በመጥፋታቸው ምክንያት፤ በተደጋጋሚ እየተገለፀ ባለበት ባሁኑ ግዜ፤ የኢህአዴግ ስርአት ባለስልጣኖች ግን ለህዝቡ
በተለይ ለድኻው ወገን የሚያስፈልጉትን መሰረታዊ ነገሮች ለሟሟላት ህዝቡ በመረጣቸው ነጋዴዎች በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲከፋፈሉ
እያደረግኩ ነኝ ቢልም፤ መሬት ላይ ግን በተቃራኒው መሆኑን የተገኘው መረጃ አስረድቷል፣
ከሁሉም ያገራችን አካባቢዎች
የደረሰን መረጃ እንደሚያመልክተው፤ አካፋፋዮች ተብለው በየአካባቢው የተቀመጡት የስርአቱ ደጋፊ የሆኑ ነጋዴዎች፤ ወደ ህዝቡ ሳይደርስ
ለግላቸው እንደሚጠቀሙበት የገለፀው መረጃው፤ በተለይ ካለፈው አመት ጀምሮ በህዝብ ተገምግሞ የተወሰደ እርምጃ ባለመኖሩ ዝቅተኛ ኑሮ
እየመሩ የሚገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች በከፋ ችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ይታወቃል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በአንዳንድ ያገራችን የገበያ ማእከሎች አንድ ኪሎ ሱኳር ከ 60 እስከ 70 ብር እየተሸጠ እንደሆነና፤ አሁን ደግሞ ጠቅልሎ በመጥፋቱ
ምክንያት፤ ሻይ ሊጠጣ የሚፈልግ ሰው እንደ አማርጭ ከረሜላን አሟሙቶ መጠጣት እንደ መፍትሄ እየተጠቀመ መሆኑን። መረጃው አክሎ አስረድቷል፣