Wednesday, October 8, 2014

በመተማ ከተማና አካባቢው የሚገኙ የፖሊስ አባላት የህዝብ ገንዘብ በመዝረፍ ስራ ላይ ስለ ተጠምዱ ነዋሪዉን ህዝብ ምሬቱን በመግለጽ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።






በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በሰሜን ጎንደር መተማ ሽሀዲን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የፖሊስ አባላት። በማታ ሲንቀሳቀስ ያገኙትን ሰለማዊ ሰው  ገንዘብ እያስከፈሉት መሆናቸውንና። ለመክፈል ፈቃደኛ ያልሆኑትን ደግሞ ሙሉ ሌሊት እየደበደብዋቸው እንደሚያድሩ ታውቋል፣
  ህገወጥ በሆኑ የፖሊስ አባላት ሰላማቸው አጥተው ያሉት እነዚህ ነዋሪዎች። መስከረም 17 2007 ዓ/ም ብሶታቸው ወደ ሚመለከተው አካል አቅርበው ሰሚ ጀሮ አጥተው ተቸግረው እንዳሉ የገለጸው መረጃው። በፖሊሶች ተደብድበው ገንዘባቸው ከተቀሙት ሰዎች መካከልም። ነብዩ አለሙና አሰግድ ፋንታሁን የተባሉት እንደሚገኙባቸው መረጃው አስታወቀ፣
    ገንዘብና ንብረታቸው በመቀማት ህዝቡን በማበሳበስ ላይ ተጠምደው የሚገኙት ፖሊሶች። ረዳት ኢንስፔክተር ተሸመ ይግዛው፤ ዋና ሳጅን መኳንንት ታፈረና ሌሎች የስራ ተባባሪዎቻቸው መሆናቸው ምንጮቻችን ጨምሮው አስርድቷል፣