በትግራይ ምእራባዊ ዞን ዳንሻ ከተማ በገዢው ህወሓት-ኢህአደግ ተደልለው ከተመደቡት የፖሊስ አባላት አንዱ
የሆነው ኮንስታብል ሕሉፍ የተባለው ፖሊስ የመምህር ታከለ ዳኘው ባለቤት የሆነች ወይዘሮ፤ መስከረም 14 2007ዓ/ም ልብስ አጠባ
ስራ ላይ በነበረችበት ግዜ፤ ተደብቆ ቆይቶ እንደደፈራት የገለጸው መረጃው፤ ባለቤትዋ መ/ር ታከለ ዳኘው በተፈጸመው ተግባር ምስክሮች አቅርቦ ለፖሊስ ክስ ባቀረበበት ግዜ፤ ሰሚ ጀሮ
እንዳጣና ወንጀል የፈጸመው ፖሊስ የሚጠይቀው አካል እንዳላገኘ ለማወቅ ተችሏል፣
የኢህአደግ ገዢ መንግስት ፖሊሶች ህግ
እንዳይጣስና ሰላም እዳይደፈርስ በአጠቃላይ የዜጎች ደህንነት ከመጠበቅ ፈንታ። ከዕድሜ በታችና ባለትዳር ለሆኑ ሴቶች የመድፈር ሁኔታም አመታት ያስቆጠረ መሆኑንና። ይህ በዳንሻ ከተማ የተፈፀመው
ወንጀልም ያለፈውን ተመሳሳይ ተግባር ማሳያ እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።