ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በሰሜን ጎንደር ዞን መተማ ከተማ ከአስር አመት በላይ በህጋዊ
መንገድ ተሰጥተው ሲጠቀሙበት የነበረውን የእርሻ መሬታቸው፤ ተገቢውን ካሳ ከመንግስት እንደሚሰጣቸው ተነግሮ ቦታው እንዲለቁ ቢደረግም፤
በባለስልጣናቱ የተገባለቸው ቃል እስካሁን ባለመተግበሩ። መፍትሄ ለማግኘት ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ እየተንከራተቱ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣
ለተወሰደባቸው መሬት ካሳ እዲሰጣቸው
በተደጋጋሚ ወደ ወረዳና ዞን ጠይቀው ስላልተመለሰላቸው። መፍትሄ ለማግኘት
ክልል ድረስ ጥያቄአቸውን ባሰሙበት ሰዓት። የወረዳው አስተዳደር ካሳ እንደከፈላቸው አስመስሎ የሃሰት ፊርማ ለክልሉ ባለስልጣናት
በማስረከቡ። የክልሉ ባለስልጣናት በበኩላቸው እንደተከፈላችሁ ነው የምናውቀው ከፈለጋችሁ እንደተከፈላችሁ የሚያረጋግጥ ፊርማችሁን
ማየት ትችላላቹ በማለት እንዳሳዩአቸው ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በችግሩ ሰለባ የሆኑት
ዜጎቻችን ደግሞ እኛ እስካሁን የወሰድነው ካሳ የለንም በአበቱታ ላይ ነው ያለነው። ይህ እያሳያችሁን ያላችሁት ፊርማ የኛ አይደለም
እራሱ የፈረመበት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ውስጣችሁን ፈትሹ ብለው መናገራቸውና። የክልሉ ባለስልጣናት ግን ገንዘቡን የወረዳው አስተዳደር ለህዝብ ብሎ ከመንግስት
ካዘና በማውጣት ለግል ጥቅሙ እንዳዋለው ቢያውቁም እስካሁን በላዩ ላይ ምንም አይነት ህጋዊ የሆነ እርምጃ እንዳልወሰዱበት ታውቋል፣
በነኝህ ሃላፊነት የማይሰማቸውና ማንነታቸውን በረሱ በግል ጥቅም በተዘፈቁ የስርዓቱ ካድሬዎች እየተንገላቱ ያሉ ንፁሃን ዜጎቻችንን ለመጥቀስ።- አቶ ንጉስ ገብሩ፤ አቶ ጥላሁን ክንዱ፤
ወ/ሮ ጥላይነሽ ወርቆ፤ የተባሉና ሌሎችም ስማቸው ለጊዜው ያልተጠቀሱ የሚገኙባቸው ሲሆኑ። እነዚህ ሰዎች ችግራቸውን የሚያዳምጥላቸው
ባለስልጣን አጥተው በመንከራተት ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከስፍራው በላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፣