Saturday, October 4, 2014

የኢህአዴግ መሪዎች በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የገዢው ፓርቲ አባላት እንዲሆኑ እያስገደዷቸው መሆናቸውን ተገለፀ።



     እነዚህ በመላው ያገራችን አካባቢዎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ባላመኑበት ተገደው የገዢው መንግስት ፓርቲ አባላት እንዲሆኑ ባለፈው ሳምንት የድርጅቱ ባለ-ስልጣኖች ባደረጉት ስበባ ላይ መወሰናቸው ለሰራተኞቹ እንዳስቆጣቸው ከተለያዩ ያገራችን አከባቢዎች የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
     መረጃው በማስከተል ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ 2007 ዓ/ም በሚደረገው ምርጫ ላይ ለገዢው መደብ መምረጥና መደገፍ እንደሚገባውና ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ የኢህአዴግ አባል መሆኑን የሚያረጋግጥ የማንነት ወረቄት እንዲይዝ እየተገደደ መሆኑን የገለጸው መረጃው ሰራተኛውም ከስራው እንዳይባረር በመስጋት ሳይወድ የመታወቅያ ካርዱን እየወሰደ መሆኑን ተገልጿል።
     ዜጎችን ያለፍላጎታቸው እያስገደድክ የኢህአዴግን አባላት እንዲሆኑ እየተከተሉት ያለውን መንገድ የስርአቱን ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ አጉልቶ የሚያሳይ እንደሆነና ህዝቡን በሰፊው እየተነጋገረበት መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድተዋል።