Thursday, October 9, 2014

የኢህአደግ መከላከያ ሰራዊት የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች። ብውስጣቸው ያለውን ችግር ለመፍታት በሚል ምክንያት። ስፊ ግምገማ እያካሄዱ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለጹ፣





በአሁኑ ግዜ በኢህአደግ መከላከያ ሰራዊት የበላይና የበታች አመራር መኮንኖች። በመካከላቸው ውስጥ ያለውን ስር የሰደደ መቃቃር። ለስርአቱ ሃላፊዎች እያስጨነቃቸው ለቆየው ችግር። አሁን እንፈታው በሚል ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣
    በስብሰባው ውስጥ እንዲታዩ ተብለው ከመጡት ነጥቦች ለመጥቀስ ያህል።. ለገዢው ስርአት አስጊ ናቸው ለሚልዋቸው ሰዎች መያዝ፤ ለስርአቱ የማይደግፉና የማይቃወሙ አቋማቸው ምን እንደሆነ የማይታወቁ ሰዎችን መለየት፤ ያለ ስራ  በተለያየ ፅ/ቤቶች በሃላፊነት የተቀመጡትን ማስወጣት፤ በእድገትና ሌላ ምክንያቶች ለመከላከያ ድጋፍ የማይሰጡ የሚልዋቸውን እንዲወገዱ በማለት በሃይለኛ ስበሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል፣