እንደምንጮቻችን መረጃ
መሰረት። በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ናዕዴር ዓዴት ወረዳ። አበባ ዮሃንስ ቀበሌ አስተዳዳሪ የነበረ ተክለ ሞገስ የተባለ ካድሬ የኑሮ
ችግር ላለባቸው እንዲውል ተብሎ ከለጋሽ ድርጅቶች የተገኘ የእርዳታ እህል እና ገንዘብ በሚገባው ቦታ ሳይውል አየር በአየር እየሽጠው
እንዳለ በቀበሌዋ ነዋሪ ህዝብ ከሃላፊነቱ ወርዶ በህግ እንዲጠየቅ በተደጋጋሚ ተገምግሞ አቤቱታ ከቀረበበት በኋላ። የወረዳዋ ባለስልጣናት
ግን ከግለሰቡ ጋር በጥቅማጥቅም ላይ የተመሰረተ ትስስር ፈጥረው ስለቆዩ። የሚያገኙት ጥቅም እንዳይቋረጥባቸው ስለፈለጉ ከሃላፊነቱ
እንዳይወርድ እየተከላከሉለት መሆናቸውን አስረድቷል፣
መርጃው ጨምሮ
እንዳስረዳው።- የቀበሌዋ ነዋሪዎች አቤቱታ በአግባቡ አቅርበው በወረዳው አስተዳዳሪዎች ሊሰሙ ስላልቻሉና። ባለፈው ሳምንት በአስተዳዳሪዎች
ላይ ተቃውሞ ስላነሱ። በቀበሌዋ አስተዳዳሪ ምትክ ተክለ አፅብሃ የተባለ
ዘራፊ መሾማቸውን የገለፀው መረጃው። ከህዝብ አፍ እያወጣ ሲበላ የቆየ አቶ ተክለ ሞገስ ግን። በህግ ሳይጠየቅ እንደቀረ ለማወቅ
ተችሏል፣