Thursday, October 9, 2014

የኢህአዴግ ገዠው መንግስት ካድሬዎች በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች ለሚገኙ የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን እየሰበሰቡ ስለመጭው ምርጫ አስመልክተው ቅስቀሳ ባደረጉላቸው ሰዓት ተማሪዎቹ ተቃውሞ እንዳሰሙ ተገለፀ፣





እነዚህ ትምህርታቸውን አቋርጠው በግዴታ ስብሰባ ላይ ተጠምደው የሚገኙ የ10 እና 12 ክፍል ተማሪዎች። 2007 ዓ.ም ለሚደረገው አስመሳይ ምርጫ ኢህአዴግን እንዲመርጡ በስርዓቱ ካድሬዎች ቅስቀሳ እየተደረገላቸው ቢሆንም። እነዚህ በግዴታ የተሰበሰቡ ተማሪዎች ግን የትምህርት ጊዜአችንን አታባክኑብን። ይህ ትምህርት ቤት እንጂ የስርዓቱ የፖለቲካ ማስፈፀሚያ መድረክ አይደለም በማለት በስርዓቱ የቀረበላቸውን አጀንዳ እንደተቃወሙት ከተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች በተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፣
   መረጃው አክሎ።- እነዚህ ተማሪዎች ተገደው በተሰበሰቡበት ሰዓት የሰጡት ሓሳብ እናንተ የኢህአዴግ መሪዎች ናችሁ ሃገራችንንና ህዝባችንን እየረበሻችሁ ያላችሁ። በተግባር በማይታይ አስመሳይ ዴሞክራሲ። ሃገር እንድትበታተን በሚፈቅድ አንቀፅ 39ን በህገ መንግስታችሁ ውስጥ በማስፈር፤ ወንጀል ላልፈፀሙ ታጋዮችንና የተቃዋሚ ድርጅቶች አሸባሪዎች እያላችሁ የምትገድሉ፤ኢ-ዴሞክራሲያዊ በሆነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ ለሚታገሉ ድርጅቶች። እንቅፋት በመሆናችሁ ምክንያት ነው በረሃ ገብተው የትጥቅ ትግል እንዲያደረጉ ተገደው ያሉ” የሚሉና ሌሎችን ለስርዓቱ የሚነቅፉ አስተያየቶች በመስጠት። ስርዓቱን እየተቃዎሙት እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው አስታውቋል፣