በቃፍታ ወረዳ ልዩ ቦታ ሰግሊን በተባለ አካባቢ የሚገኙ ታጣቂዎች፤ አስተዳዳሪዎች፤ ሚሊሻዎችና ፖሊሶች እርስ
በራሳቸው እየተገዳደሉ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው። የመገዳደሉ መነሻም የቀበሌዋ አስተዳዳሪ ዳኘው ምሩፅ ከሚሊሻ ተስፋይ ገዛሃኝ
ጋር አንድ ላይ በመሆን፤ አቶ ተስፋለም ጎይቶኦም ለተባለ ምሊሻ ትጥቅህን አራግፍ ባሉበት ሰዓት፤ ጥፋቴን ሳትነግሩኝ ትጥቄን አላራግፍም
የሚል መልስ ስለሰጣቸው፤ በመካከላቸው በተፈጠረው አለመረዳዳት እርስ በርሳቸው በያዙት መሳርያ ተታኩሰው እንደተገዳደሉ ለማወቅ ተችሏል።
በአስተዳደሩ የተበላሸ አሰራር ምክንያት
የተናደደው ተስፋለም ጎይቶም፤ ካስተዳደሩ ጋር ወግነው ለነበሩ ሁለት ፖሊሶች መስከረም 7/2007 ዓ.ም በጥይት ተኩሶ በመግደል
ከቦታው እንደተሰወረ ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል።