Sunday, November 2, 2014

የትግራይ ክልል ባለ-ስልጣናት የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላት ከራሳችን ፋብሪካ ስኳር ማቅረብ ችለናል በማለት በቅርብ ጊዜ የለቀቁት ወሬ ፍፁም ከሃቅ የራቀ እንደነበር ምንጮቻችን ገለፁ፣




የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በቅርብ ጊዜ በሚዲያዎቻቸውና እራሳቸው ባዘጋጁት መድረክ ቀርበው ከራሳችን ፋብሪካ ያፈራነውን ከ10 ሽህ ኩንታል በላይ ስኳር ለህዝባችን በማቅረብ የተፈጠረውን የስኳር እጥረት ለማረጋጋት ችለናል ሲሉ የሰጡት ሓሳብ ፍፁም ሐሰት መሆኑን ምንጮቻችን አስታወቁ፣
    እንደምንጮቻችን መረጃ የስርዓቱ ባለስልጣኖች ስኳር ከራሳቸው ፋብሪካ እንዳመረቱት አድርገው እየተናገሩት ያለው ወሬ ፍፁም ትክክለኛ እንዳልሆነና ይህ አምርተነዋል የሚሉት ስኳርም ስርዓቱን ከሚደግፉ ካድሬዎችና መሰሎቻቸው ከሆኑት ሃብታሞች በተለያየ መንገድ አስቀምጠውት የነበረ እንደሆነና፤ ህዝቡ ተቃውሞ እንዳያስነሳብን ተሎ እርዱን ስለተባሉ፤ ከየመጋዝናቸው ሰብስበው ያቀረቡት እንደሆነ ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል፣