በምንጮቻችን መረጃ መሰረት
የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ካለፉት ጊዜያት በከፋ መልኩ ከጥቅምት 18 /2007 ዓ/ም ጀምሮ በሁሉም የከተማው አከባቢ ህዝቡ የሚጠጣና
ለምግብ ማብሰያ ውሃ አጥቶ ተቸግሮ ባለበት በአሁኑ ግዜ። ወደሚመለከታቸው አካላት በተደጋጋሚ አቤቱታ ባቀረበበት ግዜ የከተማዋ አስተዳደሮች
ግን ጥያቄውን ሰምተው የወሰዱት እርምጃ እንደሌለ ታወቀ፣
አጋጥሞ ባለው የውሃ እጥረትና ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃ ምክንያት፤ በዝቅተኛ
እድሜ ላይ የሚገኙ ሕፃናት በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጠቁ የገለፀው መረጃው፤ የከተማዋ ባለሃብቶችም ከክልተ አውላዕሎ፤ ገረብ ግባና
ማይ መኽደን አከባቢዎች በመኪና እያስመጡ በመጠቀም ላይ መሆናቸውና ድሃው ህብረተሰብ ግን መፍትሄ አጥቶ በከባድ ችግር ላይ ወድቆ
እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣
