Monday, December 29, 2014

ሙስና መለያው በሆነው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት የተማረሩ የመንግስት ሰራተኞች በፈቃዳቸው ስራቸውን እየለቀቁ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።



   በሙስና የተጨማለቀው ገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ቡድን እየተከተለው ያለው አሰራር ያሰጋቸው በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን እየለቀቁ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ስራቸውን እየለቀቁ  ከሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች መካከል በአዲግራት ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ ዘርፍ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የቆየው አቶ ፍፁም እንዲሁም የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ አቶ ኤልያስና ሌሎችም የሚገኙበት እንደሆኑ ታውቋል።
      መረጃው ጨምሮም  እነዚህ ዜጎች ከስራቸው እንዲለቁ ከሚያስገድዳቸው ምክንያት በዞኑ የሚገኙ ከፍተኛ ሃላፊዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሚሰጥዋቸው ስርዓት ያልተከተለና በተዛባ ትዕዛዛቸው ለሚፈፀም ብልሹ አስተዳደር በታችኞች ሰራተኞች እንደተፈፀመ እያስመሰሉ በሚያካሂዱት የስብሰባ ግምገማ ሰራተኞችን እያበሳበሷቸው በመሆናቸው ባልዋሉበት እየተጠቆሙና እየታደኑ በመታሰር ላይ እንዳሉ የታዘቡ ሰራተኞች የእነሱ እጣ ፋንታ እንዳይደርስባቸው እየወሰዱት ያለ እርምጃ መሆኑ ታውቋል።