በክልሉ የሚገኙ ከ340 በላይ የሀገር ውስጥ
ባለሃብቶች በነፍስ ወከፍ ዝቅተኛው 500 ሄክታር ከፍተኛው ደግሞ 1500 ሄክታር መሬት እንዲሰጣቸው በተለያዩ የድርጅትና የግለሰብ
ስሞች ያቀረቧቸው ማመልከቻዎች የመጨረሻ የእውቅና መስጫ ተቋም ወደ ሆነው የአካባቢ ጥበቃ ፅህፈት ቤት ከደረሰ በኋላ የማስፈፀሚያ
በሚል ስም ጉቦ እንዲከፍሉ በግልፅ ተጠይቀው ባለመክፈላቸው ሊዘገይ እንደቻለ ለማወቅ ተችሏል።
በግልፅ ሙስና
የተጠየቁት ከበርታ ብሄረሰብ ውጭ የሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ
ዜጋ በሙስና መልክ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲሰጡ በግልፅ መጠየቃቸውን የገለፀው መረጃው በተለይ ይህ እየሆነ ያለውም ድሃ አርሶ አደሮች
እያለሙት ያለውን መሬት እየተቀሙ ከውጭ ለመጡ ከ38 በላይ ባለሃብቶች በቅድሚያ ያለምንም የማስፈፀሚያ ክፍያ ቦታው እንዲሰጡ ተደርጓል
ሲሉ ነዋሪዎቹ በምሬት ገልፀዋል።