በአብቁተ የጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርቶ ኑሮውን ይመራ የነበረው አቶ
አበበ ገድፍ የተባለው ግለሰብ የካቲት 10 /2007 ዓ/ም
ለዘረፋ በሌሊት የመጡትን የፅህፈት ቤት ሃላፊዎች በዕዳ እንዳያስጠይቁት
በተደጋጋሚ እንዲመለሱ ቢነግራቸውም አሻፈረኝ በማለት የገንዘብ ማስቀመጫ ካዝናውን በሃይል ሊከፍቱ ሲሞክሩ በክላሽ ኮፍ መሳሪያ እያንዳንዳቸውን በሁለት
ጥይት ተኩሶ እንደገደላቸውና ወዲያውኑ ከቦታው እንደተሰወረ መረጃው አስታውቋል።
በስርቆት
ስራ ላይ የተሰማሩ የገዥው መንግስት ተላላኪ የፅህፈት ቤት ሃላዎችን በጥይት እሩምታ የገደለው አቶ አበበ ገድፍ ከፍተኛ የህዝብ
ተቀባይነትና ድጋፍ እንዲሁም አድናቆትን በማግኘቱ የተናደዱ የመንግስት ካድሬዎች ግለሰቡ የተወለደበትን ሳንጂ የተባለውን አካባቢ በማሰስ ላይ መሆናቸውን ምንጮች ጨምረው
አስረድተዋል።