Sunday, March 15, 2015

የህወሓት-ኢህአደግ ባለስልጣናት ስጋት የሆኑባቸውን የቀድሞ ታጋዮች ማባበያ የሚሆን የተወሰነ ገንዘብ በመስጠታቸው ምክንያት ምንም ገንዘብ ያላገኙ የቀድሞ ታጋዮች በሃይለኛ ስሜት ውስጥ እንዳሉ ተገለፀ፣



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን የሚገኙ የቀድሞ የህወሓት ታጋይ ዜጎቻችን ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኝነት ፈጥረው ከስልጣናችን ሊያወርዱን ይችላሉ የሚል ስጋት ያደረበት ገዢው የኢህአዴግ ስርአት በልዩ ሁኔታ የሚሰጋባቸውን የተወሰነ ገንዘብ እያደላቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው ምንም ችግር አያመጡም ብሎ ያልሰጣቸው ታጋዮችም ሁላችን ለፍተንና ተንከራትተን ስናበቃ ለምንድ ነው በገንዘብ ልዩነት የሚደረገው በማለት በከባድ ስሜት ውስጥ ገብተው እንደሚገኙ ታውቋል፣
   መረጃው ጨምሮ እንደገለፀው እነዚህ በተለያዩ ወቅቶች የግል ኑሯቸውን በመተው ከህወሓት-ኢህአደግ ጎን ተሰልፈው በዱርና በገደል ሲንከራተቱ የቆዩ ታጋዮች በስርአቱ ያለምንም እገዛ  ተጥለው የቆዩ ሲሆን አሁንሞ አድልዎ እየተፈፀመባቸው ባሉት ነባር ታጋዮችና በስርአቱ ካድሬዎች መካከል ሃይለኛ አለመግባባት ተፈጥሮ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል፣