በምንጮቻችን
መረጃ መሰረት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የሚገኙ የህወሃት-ኢህአደግ ካድሬዎች ላለፉት 24 ዓመታት ትኩረት ስጥቷቸው የማያውቁትን የሰማዕታት
ቤተሰቦች ምርጫ ስለተቃረበ በህዝብ ተቀባይነት ለማግኘት ሲሉ ለተወሰኑት የሰማዕታት ቤተሰቦች ገንዘብ እየሰጡ በማባበል ስራ ላይ
መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
በካድሬዎቹ
ከፋፋይ አካሄድ የተቆጡት የሰማዕታት ቤተሰቦችም አንድ ታጋይ የተሰዋበት ቤተሰብ እገዛ ሲደረግለት እስከ አምስት ልጆቹን ያጣ ቤተሰብ
ግን የሚያየው አካል እንዳላገኘና ለአንድ ዓይነት አላማ ብለው አንድ አይነት ደም አይደለም ወይ ያፍስሱትና የተሰዉት የሚሉ ጥያቄዎች
በሰማታት ቤተሰቦች እየተነሱ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ወላጆች በልጆቻቸው መስዋዕትነት መከበር ሲገባቸው በስርአቱ ከፋፋይ አካሄድ
ምክንያት በከፍተኛ ሃዘን ተውጠው እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣