Sunday, March 15, 2015

በራማ ከተማ ውስጥ በህዝቡ ላይ ግፍ ሲያወርዱ የቆዩ የኢህአዴግ የፖሊስ አባላት መገደላቸውን ምንጮቻችን ከከተማው አስታወቁ፣




በመረጃው መሰረት በትግራይ ማዕከላዊ ዞን፤ ራማ ከተማ ውስጥ ንፁሃን ወገኖችን ሲያሰቃዩ የቆዩ የስርዓቱ አገልጋይ ፖሊሶች እየተገደሉ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ከተገደሉት ፖሊሶች ለመጥቀስ ያህልም ተክላይ የተባለና አንድ ሌላ ለግዜው ስሙ ያልታወቀ ፖሊስ በጸረ ህዝብ ተግባራቸው የተበሳጨው ወጣት የካቲት 9/2007 ዓ/ም እንደገደላቸውና በተጨማሪም ለአንድ ፖሊስ በጥይት ተኩሶ በማቁሰል ከቦታው እንደተሰወረ ለማወቅ ተችሏል፣
     የሟቹ ፖሊስ ተክላይ አስከሬን የካቲት 10/ 2007 ወደ ተወለደበት ዓብይ ዓዲ ከተማ ተወስዶ መቀበሩንና ሁለተኛው ለጊዜው ስሙ ያልታወቀው ሟችም ወርዒለኸ ወረዳ ፀድያ ወደ ተባለው ቦታ ተወስዶ የቀብር ስነስርዓቱ እንደተፈጸመ፤ ሶሦስተኛው ግለሰብም በጥይት ተመቶ ክፉኛ በመጎዳቱ ምክንያት ስቃይ ላይ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስርድቷል፣