በመረጃው
መሰረት ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ አሕፈሮም ወረዳ ወደ ፈረስማይ ከተማ ለስራ የተላኩት ሁለት የስርዓቱ የፖሊስ አባላት የካቲት
7/ 2007 ዓ/ም ሰርግ ላይ የነበረውን ወጣት በወንጀል በክስ ትፈለጋለህ ብለው አስረው ለመውሰድ በሞከሩበት ጊዜ የሰርግ ስነ-ስርዓት
እየፈጸመ የነበረው ወጣት በበኩሉም ፖሊሶቹን ገድሎ እንዳመለጠ ለማወቅ
ተችሏል፣
የተገደሉት ሁለት የፖሊስ አባላት ፀጋይ ታደሰና ተክላይ ሃይሉ የተባሉ
ሲሆኑ። ገዳዩ ከፈረስማይ ፖሊሶች እጅ ስላመለጠ በሱ ምትክ ሰርግ ላይ የነበሩትን በርካታ ሰዎች አስረው መውሰዳቸውን የገለፀው መረጃው
የታሰሩበት ቦታ ጥበት ስላጋጠማቸው በግለሰቦች ቤት ሳይቀር አስረው እያሰቃዩዋቸው እንደሚገኙ መረጃው አስታውቋል፣
በተመሳሳይ በትግራይ ምእራባዊ ዞን፤ ዳንሻ ከተማ ውስጥ ሁነው የተባለ ወጣት የካቲት 12/2007 ዓ/ም ምሽት 3።00። በህዝብ ላይ የተለያዩ ግፎችን ሲፈፅም ለነበረው
አታላይ የተባለውን የዳንሻ ከተማ ፖሊስ በዱላ ደብድቦ እንደገደለው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣