ምንጮቻችን
ከከተማዋ በላኩት መረጃ መሰረት የሸራሮ ከተማ አስተዳዳሪ ብሩኽ ዘፈሩ የካቲት 7/ 2007 ዓ/ም የሸራሮ ከተማ ነዋሪዎችን ሰብስቦ
የየካቲት 11ን በዓል አከባበርና በመጪው ግንቦት ወር 2007 ዓ/ም የሚካሄደውን አስመሳይ ምርጫ በተመለከተ ቅስቀሳ በጀመረበት
ግዜ ተሰብሳቢው ህዝብ ንግግሩን በመቃወም “ህጋዊነት በሌለው መንገድ
ታፍነው የተወሰዱ ንፁሃን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አድራሻቸው ሳይነገረን ያንተን ንግግር ልንሰማህ ፍቃደኞች አይደለንም” በማለት
ሃሳቡን ውድቅ እንዳደረጉት ሊታወቅ ተችሏል፣
በስርዓቱ ታፍነው
ከተወሰዱትና አድራሻቸው ካልታወቁ ወገኖቻችን በስብሰባው ስማቸውን
ከተገለፁት የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል አማረ በላይ፤ ነጋሲ አድሃኖምና ሌሎችም ሲሆኑ ስብሰባውን ይመራ የነበረው የወረዳዋ አስተዳዳሪ
ባጋጠመው ተቃውሞ ተቆጥቶ ዛሬ ይሁን ነገ እኛን ተቃውሞ ለሚንቀሳቀስ ምህረት የለንም ለራሳችሁም የሚያድናችሁ እንደሌለ እወቁ ሲል
እንደዛተባቸው ሊታወቅ ተችሏል፣