Thursday, April 2, 2015

በዚህ ሳምንት በማዕከላዊ ዕዝ ውስጥ ሲካሄድ የቆየውን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መከላከያ ሰራዊት ስብሰባ ተከትሎ ከ30 በላይ የሚሆኑ ወታደሮች ያለምንም መሸኛ እንደተባረሩ ተገለፀ፣



ከመከላከያ ሰራዊት ባገኘነው መረጃ መሰረት በማዕከላዊ ዕዝ ሲካሄድ የቆየው ስብሰባ ለአመታት ሲያገለግሉ የቆዩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከጠላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፤ በመተባበርና  ገዥውን መንግስት በማጥላላት። በመከላከያ ስራዊቱ ውስጥ አመፅ እንዲቀሰቀስ አነሳስታችኋል በሚል የውሸት ውንጀላ ምክንያት  ከ30 በላይ የሚሆኑ ወታደሮችን ያለምንም መሸኛ እንደተባረሩ ለማወቅ ተችሏል፣
   በተመሳሳይ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ። በየደረጃው ያለው ሰራዊት ለምን ይከዳል በሚልና ጠላት ብለው በሚፈርጅዋቸው አካላት ያተኮረ ግምገማዊ ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን። ባለፈው የዜና እወጃችን መዘገባችን ይታወቃል፣