በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አዲግራት ከተማ የሚገኙ የ3ኛ አመት የማኔጂመንት ተማሪዎች በዩንቨርሲቲው ውስጥ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮች
ፍትህ እንዲያገኙ በሚል መቃወማቸውን ተከትሎ የመንፈቀ አመቱ ውጤታቸው “ሲ” ተብሎ በሃላፊዎች በተነገራቸው ሰዓት። ተማሪዎች በበኩላቸው
የፖለቲካችሁ መሳሪያ አታድርጉን በማለት በመቃወም ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣
እነዚህ ተማሪዎች
በላያቸው ላይ እየተፈፀመ ባለው ሞራላቸውን የሚነካ ተግባር ሳይደናቀፉ። ከዚህ በፊት ሲያነሷቸው የነበሩትንና አሁንም ያልተፈቱላቸውን
ጥያቄዎች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የፈጠራቸውን መሰል ተዛማጅ ችግሮች በማንገብ። እንደ ንፁህ
ውሃ እጥረት፤ ንፅህናውን ያልተጠበቀ ምግብ። የመብራት መቆራረጥና ሌሎችን በመጠየቅ ላይ ስለሚገኙ። በዚህ የተነሳም ተማሪዎቹ ከዶክተር
ዛይድና ከሌሎችም ሃላፊዎች ጋር በከባድ ውጥረት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችላል፣