Thursday, April 2, 2015

በአማራ ክልል የሚገኙ የስርዓቱ ባለስልጣናት በላያቸው ላይ እየተወሰደ ያለው ህዝባዊ እርምጃ ስጋት ስለፈጠረባቸው በህጋዊ መንገድ ለታጠቁት ሰዎች ዳግመኛ እንዲመዘገቡ እያስገደዷቸው እንደሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ፣



    በአማራ ክልል በሁሉም ወረዳዎችና ዞኖች በስርዓቱ ፍቃድ የግል ትጥቅ ያላቸውና መሳሪያ የታደላቸው ሰዎች መጋቢት 22/2007 ዓ/ም የታጠቁትን መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ ከክልሉ አዲስ መመሪያ የወረደ ሲሆን፣ የዚህ ምክንያትም የኢህአዴግ ባለስልጣናት በህዝብ ዘንድ ተቀባይነታቸው በማሽቆልቆሉና። ህብረተሰቡ በላያቸው ላይ  እርምጃ እየወሰደ በመሆኑ የፈጠረባቸው ስጋት እንደሆነ የደረሰን መረጃ ገልጿል፣
    ይህ በእንዲህ እንዳለ እነዚህ የክልሉ አስተዳዳሪዎች ሊነሳ የሚችለው ህዝባዊ አመፅ እያሰጋቸው በመሄድ ላይ ስለሚገኝ። ያለ ፍርድ ቤት ፍቃድ የታጣቂዎች መኖሪያ ቤት በስርዓቱ ካድሬዎች እየተፈተሸ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው። በዚህም የተነሳ ህዝቡ ዋስትና አጥቶ ዕለታዊ ስራው ማሳለጥ እንዳልቻለ ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ አክሎ አስረድቷል፣