Tuesday, April 7, 2015

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰላ ከተማ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እየታሰሩ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



    ከስፍራው የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን የአምባገነኑ ገዥ መንግስት ተላላኪ ፖሊሶች የኦህዴድ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሰዎችን ግላዊ ጥላቻ ስላላችሁ ነው እንጂ በክልላችን ምንም ዓይነት ለተቃውሞ የሚያበቃ የመልካም አስተዳድር ችግር የለም ስለዚህ ከግለሰቦች ጋር ያላችሁን ጥላቻ በግል መረዳዳት ካልቻላችሁ ህዝብ ስትቀሰቅሱ ዝም ብለን አናይም  የፀጥታ ጉዳይ ይመለከተናል በማለት እያሰሯቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣
    እንደዚህ አይነት የውሸት ሴራ እየተሸረበ ለእስራት ከተጋለጡት ዜጎቻችን መካከል ባለፈው ሳምንት በእስር ሲሰቃይ የቆየው መልካሙ ሂርጳ የተባለ መምህር እንደሚገኝባቸው ለማወቅ ተችሏል፣