በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ሸራሮ ከተማ
ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች። ዕለታዊ ማህበራዊ ኑሮአቸውን ለመምራት የሚያስችላቸው የመሰረተ ልማት ስላልተዘረጋላቸው። በተለይ በንፁህ
የመጠጥ ውሃ፤ የመብራት አገልግሎት፤ የኔት ዎርክ መቆራረጥና ለተዛማጅ የመሰረተ ልማት ችግሮች መጋለጣቸውን የተገኘው መረጃ አስታውቋል፣
መረጃው በማስቀጠልም። መብራት በሳምንት አንድ ግዜ እንደሚመጣና እሱም
ቢሆን በተደጋጋሚ እንደሚቆራረጥ፤ የኔት ዎርክ መቆራረጥም ስርዓቱ በህዝቡ ላይ እምነት ስለሌለው። የአማራና የትግራይ ክልል ባለስልጣኖች
ወደ ድንበር አካባቢ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የግንኙነቱ ስርዓት ጠቅልሎ ስለሚዘጋ። ህዝቡ ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ ስራውን እንዳያሳልጥ
ትልቅ እንቅፋት ስለሚፈጥርበት። ነዋሪው ህዝብ ዓመታት ያስቆጠረውን ችግሩን መፍትሄ እንዲያገኝለት ብሎ ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታ
ቢያቀርብም። እስካሁን ተገቢ መልስ ማግኘት እንዳልቻለ መረጃው እክሎ አስረድቷል፣