Friday, April 10, 2015

በሽሬ ከተማ የሚገኙት የኢህአዴግ ወታደሮች። ሆቴል ውስጥ በሚሰሩ ሴት ወገኖቻችን ላይ። ከፍተኛ ግፍ እየፈጸሙ መሆናቸው ተገለፀ፣



በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚገኙ የማእከላዊ እዝ የመከላከያ ሰራዊት። በከተማው በሚገኙ ሆቴሎች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ ግፍ እየፈፀሙ እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው። የእዙ የስታፍ አባል የሆነው አስራ አለቃ አስፋው ዲዳ የተባለው ወታደር መጋቢት 8/2007 ዓ/ም  ሆቴል ውስጥ ስትሰራ የነበረችውን አልማዝ አስረስ ለተባለችው የሆቴል ሰራተኛ። ከፍላጎትዋ ውጭ ልቅ ግንኝነት ለመፈፀም ፈቃደኛ ባለመሆንዋ ብቻ። አንድ አይንዋ እንድትጠፋ ማድረጉን መረጃው አስታወቀ፣
    ይህ አይነቱ ከባድ የህሊናና የአካል ጉዳት የፈፀመውን ወታደር። ለሁለት ቀን ብቻ እንዲታሰር ካደረጉ በኋላ። በተበዳይዋ የቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ ከእስር ቤት እንዲለቀቅ መደረጉና አይንዋን የተጎዳችው ዜጋ ግን የሚከራከርላት ወገን አጥታ። ለህክምና የሚሆን ገንዘብ ባለማግኘትዋ እየተሰቃየች እንደምትገኝ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣