Friday, May 15, 2015

የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት የማዕከላዊ እዝ ከፍተኛ ሃላፊዎች ሙስናን ለማጥፋት በሚል ተከታታይ ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሰነበቱ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በመረጃው መሰረት የማዕከላዊ እዝ ከፍተኛ አመራር የሆኑ የገዥው ስርዓት ወታደሮች በሰራዊቱ ውስጥ እየተፈፀመ ያለው ብልሹ አሰራር ሊቀረፍ ባለማቻሉ ከታች እስከ ላይ የሚገኙ መኮነኖች የህዝብን ንብረትና ገንዘብ በማጠፋፋት ስራ ላይ ስላሉ በዚህ ምክንያትም መከላከያ ሰራዊቱ በከባድ አደጋ ውስጥ መግባቱ ያሰጋቸው የሰራዊቱ አመራሮች በተከታታይ ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
     ከተለያዩ ክፍለ ሰራዊት ከሚገኙ ወታደሮች በመጋቢት ወር ብቻ ያለአገባብ ከደመወዛቸው የተቆረጠ 31 ሺህ ብር በእዙ የፋይናንስ ሃላፊ እንደተጠፋፋና እንዲሁም የእዙን ነዳጅ እየሸጡ ያለአግባብ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ መኮነኖች እንዲታወቁ በሚል  ስብሰባ ቢካሄድም ለማጋለጥ ድፍረት ስላጡ ያለምንም ፍሬ ነገር እንደተበተኑ ለማወቅ ተችሏል።