እኝህ ከፍተኛ መኮንኖች ስርዓቱ ወደ ስልጣን
ከመምጣቱ በፊት ጀምረው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኃላ በአሁኑ ጊዜ የትምህርት
ብቃት የላችሁም ሙስናም እየፈፀማችሁ ነው በሚል ምክንያት ከሃላፊነታቸው እየተነሱ በሌላ ስራ የተመደቡ ሲሆን በቦታቸውም በድግሪ
የተመረቁ እጩ መኮነኖች እየተኩ መሆናቸውን ከሰራዊቱ ውስጥ የደረሰን መረጃ አስረድቷል።
መረጃው ጨምሮም
አዳዲስ መኮነኖች ስራውን የሚያውቁት በስነ ሃሳብ ብቻ እንጂ በተግባር ስለማያውቁት ለመምራት አቅም የላቸውም ሲሉ ከተራ
ወታደሮች ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች ያቀረቡት አቤቱታ ሰሚ አካል ስላጡ በስርዓቱ ላይ ያላቸው እምነት እያሽቆለቆለ
መምጣቱን ለማወቅ ተችሏል።