Saturday, May 16, 2015

በሰሜን እዝ የሚገኙ የሰራዊት አባላት ባለፈው ሳምንት በተደረገው ስብሰባ ላይ ከዚሁ ቦታ ለምን አንቀየርም የሚል ተቃውሞ ማካሄዳቸውን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



   የእዙ አመራሮች የተነሳውን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው ዛሬም ይሁን ነገ አትቀየሩም በማለት ጥያቄ ላነሱ ግለሰቦች አነሳሾች ናችሁ በሚል ከህግ ውጭ የሆነ መንገድ በእዙ ውስጥ አስሯቸው እንደሚገኙ የገለጸው መረጃው ጥያቄ ማቅረባችን ተሳስተናል ብላችሁ በሰራዊቱ ፊት ራሳችሁን ሂስ አድርጉ ተብሎው መነገራቸውን የተገኘው መረጃ ገለፀ።
   በተጨማሪም ሁለት ወታደሮች ምንም ዓይነት ችግር ሳይፈጥሩ መባረራቸውና እነዚህ የተባረሩት ወታደሮችም ለእዙ አዛዦች እናንተ ስልጣናችሁን በመጠቀም የመንግስት ገንዘብ እያጠፋፋችሁና ወታደሩን እያሰቃያችሁ ናችሁ በማለት ብሶታቸውን እያቀረቡ እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።