በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ወሎ ሰፈርና ጎጃም በረንዳ አካባቢ የሚኖሩት
የአማራ ተወላጅ ዜጎቻችን የማንነት ካርድ የሌላቸውን ሰዎች አሳደራችኋል በሚል ምክንያት የፖሊስ አዛዦች ራሳቸው በየቤቱ እየዞሩ
ከመኖሪያ ቤታቸው አስገድደው እያስወጧቸው መሆናቸውና ይህን አይነት ተግባር የምትፈፅሙትም ከተቃዋሚ ድርጅቶች ግንኙነት ስላላችሁ
ነው በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ አስረው እያሰቃዩዋቸው እንደሆኑ ተገለፀ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሚናት ሊላ የተባለችውን የጎጃም ተወላጅ የማንነት
ካርድ የሌላቸው ሰዎች ቤትሽ ውስጥ አሳድረሻል በሚል ሰንካላ ምክንያት ታስሮው እየተሰቃዩ ከሚገኙ አንዷ መሆኗንና ያለምንም ህጋዊ
ክስና ማስረጃ ለ22 ቀናት ታስራ እንደተሰቃየች የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።