Saturday, May 16, 2015

በደቡብ ህዝቦች ክልል የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በደህዴን/ኢህአዴግ ፀጥታ አካላት እየተገደዱ ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ታወቀ።



     ምንጮቻችን ከአካባቢው እንደገለፁት በደቡብ ህዝቦች ክልል ቤንች ማጂ ዞን፤ ሰሜን ቤንች ማጂ ወረዳ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በደህዴን/ኢህአዴግ የፀጥታ አካላት እየተገደዱ ትምህርታቸውን አቋርጠው በወረዳው ፍትህና ፀጥታ ሃላፊ መኮነን ሃቢዦ በተባላው የስርአቱ የበላይ ካድሬ መሪነት የፖለቲካ ቅስቀሳ  እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ተገለፀ።
    በተለይ በወረዳው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል ደጋፊዎቻችን ያልሆኑ ተማሪዎችን የያዘ ብለው የጠረጠሩትን ዋቻሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሚያዚያ 27/2007ዓ/ም ተማሪዎችን በተከታታይ ለሁለት ቀናት ስብሰባ ላይ ጠምዷቸው እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል።
     የስብሰባው አጀንዳም -በ2007ዓ/ም የሚካሄደው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ “ ተቃዋሚዎች አማራጭ ፖሊሲ ስለሌላቸው ለዴህዴግ ኢህአዴግ መምረጥ እንዳላባቸው፤ በተቋዋሚ ድርጅቶች የሚነሱ አመፆች ተሳታፊዎች እንዳይሆኑ፤ ለሚፈጠር የፀጥታ ችግር ደግሞ ከፖሊሶች ጋር ትብብር እንዲያደርጉ መምሪያ ከሰጧቸው በኋላ ተማሪዎች በበኩላቸው “ትምህርታችንን እንዳናጠና ለምንድነው ስብሰባ ላይ የጠመዳችሁን፤ የፈተና ግዜያችን እየደረሰብን ስላለ እንድናጠና ተውን፤ በፖለቲካ ውስጥ የለንም፤ ከወደቅን በኋላ ዞር ብሎ የሚያየን የመንግስት አካል የለም” በማለት ታቋውሟቸውን እንዳሰሙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።