በደረሰን መረጃ መሰረት የማዘጋጃ ቤት ሃላፊዎች የተሰጣቸውን ሰልጣን ተጠቅመው
መሬትን ያለ አግባብ በማደል ኣርግልኝ ላርግልህ በሆነ ብልሹ አሰራር በህዝቡ ላይ ተደጋጋሚ ግፎች እየፈፀሙ መሆኑን ከገለፁ በዉኃላ ሙስና ከፈፀሙ ሰዎች ውስጥ አንዱ
ተክላይ ግደይ የተባለ ሲሆን ሃላፊነቱን ያለአግባብ ተጠቅሞ ጉቦ እየሰራ እጅ ከፈጅ በህዝብ ትብብር በመያዙ ምክንያት መታሰሩን ተገለፀ።
መረጃው በማሰከተል ሃላፊነቱን ተጠቅሞ ሙሱና የፈፀመው የሁመራ የከተማ
አስተዳዳሪ ብቻ ሳይሆን በመላው ኣገሪቱ የሚታይ መጥፎና ብልሹ አሰራር
መሆኑን በመግለፅ ውጤቱ ሲታይ ደግሞ ለኣገራችን ወደ ኃላ የሚጎትት መጥፎ አሰራር እንደሆነ በረካታ ታዛቤዎች በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።