ከአከባቢዉ ያገኘነዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ፣
አህፈሮም ወረዳ የሴሮ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ፣ ወይዘሮ እልፍነሽ አባይ እንዳሉት፣ ለበርካታ አመታት እየተጠቀሙበት የቆይትን መሬታቸዉ፣ የአህፈሮም ወረዳ አስተዳዳሪዎች
ከሴሮ ቀበሌ አስተዳዳሪ ሊቀመንበር ታደሰ አስፍሃ ሁነዉ በመመሳጠር፣ ለኢንቨስት መንት ይዉላል በሚል ፍትሃዊ ያልሆነ ሃሳብ፣ ካድሬዎቹ
በሃይል ነጥቀዉ አስተዳዳሪዎቹ በራሳቸዉና በካድሬዎቻቸዉ ጥቅም እንዳዋሉት፣ ወይዘሮዋ ገለጹ።
ወይዘሮ እልፍነሽ እንዳሉት፣ የተነጠቁትን መሬታቸዉ
እስከአሁን ድረስ ተገቢ የሆነ መሰረት ልማት እንዳልተተከለበትና፣ የሚመጥን ካሳ ማግኘት እንዳልቻሉና፣ እስካሁን ድረስ በችግር ስር
ወድቀዉ እንደሚገኙ፣ ለማወቅ ተችለዋል።
በዚህ ወቅት በመላዋ ትግራይ በመሰረተ ልማት
ስም አስተዳዳሪዎችና የህወሃት ካድሬዎች፣ ከበርካታ የተቸገሩ ዜጎች መሬት እየነጠቁ፣ ሃላፊነታቸዉ ተጠቅመዉ ለግል ጥቅማቸዉ እያዋሉት
የሚገኙ በመሆናቸዉ፣ ህዝብ ምሬቱ እያሰማ እንደሚገኝ እየተገለፀ ይገኛል።
No comments:
Post a Comment