ጥቂት የማይባሉ አገሮች ካላቸው ተፈጥሮኣዊ
ፀጋና ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፥ ካላቸው የህዝብ ብዛት ጋር መሠረት በማድረግ የሚመሩበት መንግስታዊ ስርዓት ፌደራሊዝም መዋቅር በመከተል
ያልተማከለ ስልጣን እንዲኖር በማድረግ ሦስቱ የመንግስት አካላት ደግሞ ከማንኛውም አይነት ተፅዕኖና ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው በተሰጣቸው
ስልጣንና ኃላፊነት እንዲዋጡ በማድረግ የተጠያቂነት ስርዓትን በማስፈን የተደላደለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመገንባት ብሎም የስልጣን
ባለቤቱ ህዝብ መሆኑን የሚያረጋግጡበት ሒደት በተግባር ሲሰሩበት ይታያል።
በአገሪቱ የሚኖሩ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ደግሞ ባህላቸውን፤ ማንነታቸውን፤
ቋንቋቸውን እና ሐይማኖታቸውን ነፃ ሆነው እንዲያሳድጉ፤ እንዲረዳዱበት፤ እንዲዳኙበት በአጠቃላይ ግንኙነታቸውን በመረጡት ቋንቋና
ባህል እንዲሁም የቦታ አቅራቢያ ማህበራዊ ፍትህና አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል።
በአገራችንና እንደሃገራችን ባሉ ጥቂት አምባገነኖች በዴሞክራሲ አፈናና
የህግ ጥሰት ባቆረፈዷት አገር ከሆነ ግን ፌደራሊዝም በስነ ሐሳብ ብቻ የተስተካከለ ሊሆን አይችልም።
ምክንያቱም
የፌደራሊዝም መርሆች ስልጣንን ጥቂቶች የሚያክላሉበትና እንደፍላጎታቸው የሚያሽከረክሩት ሳይሆን ባለቤቱ ህዝብ መሆኑን በማረጋገጥ
ከላይ እስከ ታች የተዘረጋ መዋቅር አንዱ የሌላውን ስልጣን ሳይጋፋ ለህግና ህግን መሰረት አድርጎ ከሰራ ብቻ ነው።
ይህ በሆነበት ሁኔታ ደግሞ የተሻለ አስተዳደራዊ ቅልጣፌ ይኑር፤ የህዝብ
ተሳትፎ ይረጋገጥ፤ የህዝብን ጥያቄና ፍላጎት በቅርብ አድምጦ አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጠው አካል ያግኝ፤ ህዝቦች ራስ በራሳቸው የሚመሩበት፤
በአቅራቢያቸው የሚዳኙበት፤ባህላቸው፤ ቋንቋቸውንና ማንነታቸውን የሚያሳድጉበት በዋናነት ደግሞ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን የሚጠበቅበት
ስርዓት ይገንባ ወዘተ ከብዙ በጥቂቱ መግለፅ ይቻላል።
ዴሞክራሲን
ተፀይፎ፤ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት እየጣሱ፤የህግ የበላይነትን እየሸረሸሩ፤የፌደራሊዝም አሰራሮች ወይም ተግባሮች እንዳይተገበሩ
በማድረግ የራሱን አበሳና ገመና ሳያይ ዛሬ ላይ ፌደራሊዝምን ጥቂቶች ሃላፊነት የጎደላቸው ሰዎች እያጠቆሩት ነው በማለት እንደ አንድ
ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ለማድረግ አይገባም።
ምክንያቱም
ፌደራሊዝም የህዝብንና የአገርን ችግር ይፈታል እንጂ ራሱ ችግር አይወልድም። እንዲያውም ችግር በጥቂቶች ተማክሎ እንዳይተርፍ ለብዙዎች
ያከፋፍላል፤ ሚዛናዊ ያልሆነ የሃብት ክፍፍል እንዳይኖር የሚከታተል መዋቅር ይዘረጋል፤ያሰፋል፤ የስልጣን ባለቤት ህዝብ መሆኑን በተግባር
መረጋገጥ እንዳለበት ይስቀምጣል።
እነዚህና ሌሎች የፌደራሊዝም መርሆች ሊንሰራሩ ባለመቻላቸው የተነሳ ለችግሮች
ሁሉ ጠንቅ ሆኖ በስልጣን መንበር ላይ እየቀለደ ያለው አምባገነኑ የወያኔ ኢህአዴግን ስርዓት በማስወገድ ህዝብ የሚያምንበት ስርዓት
ለማቆም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ላይ ትግላቸውን በማቀጣጠል ላይ ይገኛሉ።
ስለዚህ ፀረ ህዝቡ የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት ኢትዮጵያ የፌደራሊዝም ስርዓት
እንድትከተልና አማራጭ የሌለው የአስተዳደር ስርዓት መሆኑን ከመግለፅ አልፎ ለተግባራዊነቱ እያበላሸውና እያደፈረሰው በመሆኑ ዛሬ
የከፍተኛ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም ይሁን ሌሎች ምሁራንን እየሰበሰበ ከኒዮ-ሊበራል ኃይሎች ጋር እያነጣጠረ የራሱን ብልሽትና ድክመት
ለመሸፋፈን እያደረገው ያለው የከሸፈ ጥረት እንጂ ዛሬም ይሁን ነገ ፌደራሊዝም በኢዮጵያውያን ላይ የሚያመጣው ችግር እንደሌለ ማወቅ
ይገባል።እንቅፋቱ ግን የፌደራሊዝም መርሆችን ለመተግበር እያደናቀፈ ያለውን አምባገነኑን የወያኔ ኢህአዴግን ስርዓት አለማስወገዳችን
ብቻ ነው።
No comments:
Post a Comment