Saturday, October 19, 2013

በጎንደር ከተማ የሚገኙ እስር ቤቶች ሃላፊዎች አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ነጻ እንለቃችሃለን በሚል ከበርካታ እስረኞች ጉቦ ተቀበሉ፣




በደረሰን ዘገባ መሰረት የእስር ቤቱ ሃላፊዎች በስራቸው የሚገኙትን እስረኞችን ዓዲሱን ዓመት ምክንያት በማደረግ እንድትለቀቁ የምትፈልጉ ከሆነ በነፍስ ወከፍ 10 ሽህ ብር ክፈሉ የሚል ነገር በዘዴ ውስጥ ውስጡን እንዲነገር ካደረጉ ብሁዋላ አቅሙ ያላቸው እስረኞች የተየጠቁትን ብር ቢከፍሉም እስካሁን ድረስ ግን ከእስር አልተለቀቁም፣
በዓዲሱ አመተ ነጻ እንወጣለን በሚል ተስፋ ቁጥራቸው 15 የሚደርሱ እስረኞች የተጠየቁትን ገንዘብ በቤተሰቦቻቸው በኩል ከፍለው ሲያበቁ ነጻ ባለመለቀቃቸው ቅር የተሰኙት የእስረኞቹ ቤተሰቦች ጥቅምት 4,2006 ዓ/ም እሚመለከተው ክፍል ድረስ በመሄድ ገንዘባችንን መልሱልን ወይ እስረኞቹን ፍትሉን በማለት ጥያቅያቸውን አቅርበዋል፣ ነገር ግን እናንተ እራሳችሁ ጉቦ በመክፈል እስረኛ ለማስወጣት መሞከራችሁ በህግ ተጠያቂዎች ናችሁ ሲል ሃላፊ ተብየው እዳስፈራራቸው ቷውቋል፣
እንፈታለን በሚል ተስፋ ገንዘብ ከከፈሉ እስረኞች መካከል
-በጋሻው ታፈረ 10 ዓመት የተፈረደበት በግድያ ወንጀል የታሰረ
-አሳምነው መላኩ 12 ዓመት የተፈረደበት በግድያ ወንጀል የታሰረ
-አንጋው ተሞላ 8 ዓመት የተፈረደበትና ወ/ሮ ከበቡ ይገኙበታል፣