Thursday, June 18, 2015

በባህር ዳር ዙሪያ አዴት ከተማ ሁለት ወድማማቾች የቀበሌውን ፀሃፊ ገድለውት ከአካባቢው እንደተሰወሩ ተገለፀ።



   በአማራ ክልል ባህር ዳር ዙሪያ አዴት በተባለች ከተማ በህብረተስቡ ላይ ከፍተኛ ግፍና ረገጣ ሲያደርስ የነበረና በፀሃፊነት ሲያገለግል የቆየ የስርዓቱ ካድሬ በቃ ባዜና ተመስገን ባዜ የተባሉ ሁለት ወንድማማቾች ግንቦት 21/ 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 3፣00 ሰዓት ላይ ከመኖሪያ ቤቱ አስጠርተው ከቤቱ እንደወጣ በጥይት ገድለውት እንደተሰወሩ የደረሰን መረጃ አመለከተ።
   ምንጮቻችን እንደገለፁት እነዚህ ሁለት ወንድማማቾች በዚህ የስርዓቱ ካድሬ ላይ የመግደል እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት ከሚፈፅማቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆጠብ በተደጋጋሚ በቤተሰቦቹ በኩል እያደረጉ በተለያየ አይነት መንገድ እያስጠነቀቁት የቆዩ ሲሆን በተለይ ደግሞ በቅርብ ጊዜ ለ23 አመታት በህጋዊ መንገድ ስንጠቀምበት የነበርነውን መሬት ስልጣኑን ተጠቅሞ ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ቀምቶ ከመውሰዱም ባሻገር የአካባቢውን ህብረተሰብም በማን አለብኝነት ሲያንገላታና ሰብዓዊ ክብሩን እያንቋሸሸ ለሆዱ እንጂ ለህሊናው የሚኖር ዜጋ ባለመሆኑ ምክንያት ይህንን የመግደል እርምጃ ለመውሰድ እንደተገደዱ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ከአከባቢው ገልፀዋል።