ስራ ብናገኝ በሚል ተስፋ በየመንግስት መስሪያቤቱ ክፍት የስራ ቦታ የሚለጥፍባቸው ቦርዶችን ለማየት የሚሄዱ
ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ስራ ፈላጊዎችን በመከታተል ከ 3-5 ሽህ ብር ከከፈሉ ያለምንም ችግር ስራ ማግኘት እንደሚችሉ
በደላሎች በኩል በማግባባትና ከሃላፊዎች ጋር በመገናኘት የተጠቀሰውን ብር ከፍለው እንደሚቀጠሩ ከክልሉ የተለያዩ ከተሞች የደረሰን
ዘገባ ያመለክታል፣
በተለይም በመቐለ ከተማ አቶ ሃፍቶም የተባለ በመንግስት ተቋማት የሚሰራ ባለስልጣን ለራሱንም ሆነ ለሌሎች
ሙሰኞች ደላላ በመሆን ከተለያዩ መ/ቤቶች ሃላፊዎች ጋር በመገናኘትና ክፍት የስራ ቦታዎችን በማጥናት ከስራ ፈላጊዎች ጉቦ ይቀበላል፣
ከላይ የተጠቀሰው መጠን ገንዘብ ከፍለው በመንግስት ሰራተኝነት የተቀጠሩ ግለሰቦችን ለመጥቀስ በዓፋር ክልል
የተመደበው አቶ አበበ ተጫነና ከደሴ አከባቢ የመጣች አስካለ አማረ ይገኙበታል፣