በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአዊ ዞን በሚገኙ የወረዳ ፅሕፈት ቤቶች ውስጥ ለቀጣዩ ምርጫ እንዲያስፈፅሙ ተብለው፤ ከያንዳንዱ ጽ/ቤት 5 የደህንነቶች አባላት
እንደተመደቡ ለማወቅ ተችሏል፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአንከሻ ወረዳ ውስጥ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት
ውስጥ ከሚሰሩ፦ አቶ ዘመነ፤ አቶ አንተነህና አቶ አሰፋ፤ ከማህበራት ደግሞ አቶ አማኒኤል፤ ከእርሻ ጽ/ቤት አቶ ሃሰንና አቶ መለስ
የተባሉት እንደሚገኙባቸው የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል፣
በተጨማሪ በቦታው የሚገኙት የብአዴን ኢህአዴግ አባላት ለተቃዋሚ ድርጅት
አባላቶች ማስፈራራታቸውን የገለፀው መረጃው። በስርዓቱ ካድሬዎች የማስፈራራት ዛቻ ከደረሰባቸውም አቶ ተፈሪ የተባሉት የመኢአድ አባል
እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል፣