Friday, January 30, 2015

በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ የሚገኙ የምልሻ አባላት እየተሰጠ ያለውን ሃላፊነት የጎደለው ወታደራዊ ስልጠና የኑፁሃን ሰዎችንና እንስሳዎችን ህይወት እየቀጠፈ መሆኑ ተገለፀ።



እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል፤ ምስራቃዊ ዞን፤ አፅቢ ወንበርታ ወረዳ፤ ሓየሎም ቀበሌ ልዩ ስሙ ቀጸሎ በተባለው አካባቢ በገዢው ብዱን ባለስልጣኖች ለነዋሪው ህብረተሰብ ሳያሳውቁ ጥር 6 /2007 ዓ/ም የጀመሩት የምልሻ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት እስከ አሁን  ድረስ አቶ ሕሸ ገብሩ የተባለው አርሶ አደር የሚገኙባቸው ሰዎችና በርከት ያሉ እንስሶች እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።
 እንዲህ ያለ ሃላፊነት የጎደለው የምልሻ ማሰልጠን ተግባር። በሁሉም የትግራይ ዞኖች እየተካሄደ እንዳለና በሰው፤ በእንስሳትና በንብረት ላይም ከፈተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ከኣካባቢው የደረሰን መረጃ አስረድቷል።