Friday, February 1, 2013

በ1993 ዓ/ም በህወሓት ውስጥ የታየው የመሰነጣጠቅ አደጋ ዳግም ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት እየተጠናከረ መምጣቱ ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት የህወሓት አመራሮች ባለፈው ወር በመቐለ ከተማ ባካሄዱት ስብሰባ እነ ስዩም መስፍን ፤ አባይ ጸሃየ ፤ ጸጋይ በርሀ ቁዱሳን ነጋና አባይ ወልዱ ህወሓት ተዳክሞ የኅሊት እየሄደ ስለሆነ በ 1993 ዓ/ም ከድርጅቱ የተባረሩት እነ አቶ ስየ አብረሃ ፤ ገብሩ አስራትና ሌሎችም ወደ ድርጅቱ እንዲመለሱ ቢደረግ ይሻላል ሲሉ ያቀረቡት ሃሳብ አብዛኛዎቹን የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴዎች እንዳላስደሰተና በመካከላቸውም ውጥረት መስፈኑን ለማወቅ ተችለዋል፣
በቀረበው ሃሳብ ቅር ከተሰኙት የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴዎች መካከል አዜብ መስፍን ፤ አርከበ ዕቑባይና ቴዎድሮስ ሓጎስ የሚገኙበት ሲሆን ሰማእታትን ረግጠው የወጡትን አሁን ዳግም ወደ ድርጅቱ እንዲመለሱ መጠየቃችሁ በራሱ እናንተንም ጭምር ከድርጅቱ እንድትባረሩ የሚገፋፋ ነው ብለው ሲናገሩ በስብሰባው መደመጣቸውንና በህዝቡም ውስጥ በራሪ ወረቀቶችንም መበተናቸውን ለማወቅ ተችለዋል፣
ከትግራይ ህዝብ ተነጥለው ብቻቸውን ከቀሩ 22 ዓመታት ያስቆጠሩ የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው እየታየ ያለውን የመሰነጣጠቅ ዓደጋ እራሳቸው መፍታት ሲያቅታቸው እንደተለመደው ወደ ህዝቡ ማውረድ የማይቀር ነገር ቢሆንም ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለው ያለ የመቐለ ከተማ ህዝብ ግን ሌላ የኛ የምንለው የተሻለ አማራጭ መያዝ እንጂ ከእንግዲህ ከነዚሁ ጋር የምንወግንበት ነገር አይኖርም ሲል ይደመጣል፣