Wednesday, February 11, 2015

የሽሬ ከተማ ነዋሪ ህዝብ 40ኛው የካቲት 11 የህወሓት ልደት በአል የሚውል ገንዘብ አዋጡ እየተባለ በህወሓት ካድሬዎች እየተገደዱ እንዳሉ ታወቀ።



የሽሬ እንዳስላሴ ነዋሪ ህዝብ የየካቲት 11 በአልን ለማክበር ገንዘብ እንዲያዋጣ በህወሓት ካድሬዎች ጥር 17/ 2007ዓ/ም ሲጠየቅ መዋሉ የገለጸው መርጃው ህዝቡ ደግሞ ከልክ በላይ የተወሰነልን ግብር የነበርንን ንብረት ሽጠን የከፈልነው ሳይበቃ አሁን ደግሞ ለጭፈራና ለዳንኬራ የሚሆን ገንዘብ ልናዋጣ መጠየቃችሁ ምን ያህል በዝበዦች መሆናችሁ አውቀናችኋል በማለት አንከፍልም እያሉ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ነዋሪዎችን መሰረት በማድረግ የህወሓት ካድሬዎች ከጥር 17 2007ዓ/ም ጀምሮ ባንዴራ ግዙ እያሉ በባንዴራ ንግድ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ከገለፀ በኋላ አልገዛም ያለው ሰው ደግሞ የባንዴራ ፀርና፤ የህልውና ፀር፤ ፀረ ሃገር ወዘተ በማለት ህዝብ በማስፈራራት እያጨናነቁት እንዳሉ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።