Tuesday, June 16, 2015

ሰሜን እዝ ከሚገኙ የሰራዊት አባላት ኢህአዴግ በምርጫ ስላሸነፈና ግንቦት 20 በዓልን በደመቀ መንገድ ለማክበር ተብሎ ከእያንዳዳቸው በአስገዳጅነት ከወር ደመወዛቸው 125 ብር እንደተቆረጠባቸው ተገለጸ።



   በደረሰን መረጃ መሰረት በሰሜን እዝ በተለያዩ ክፍለጦሮች የሚገኙ የሰራዊት አባላት ኢህአዴግ ምርጫውን ስላሸነፈና የግንቦት 20 በዓልን ለማክበር በሚል ከሰራዊቱ ፍላጎት ውጭ በሆነ መንገድ ከእዙ ወታደራዊ ክበብ ለሁሉም ክፍለጠሮች የሚሆን 12,625,836 ብር ወጪ አድርገው እንደተጠቀሙበት  ለማወቅ ተችሏል።
   ይህ ያለምንም ፈቃድ ከእያዳንድ ወታደር ከግንቦት ወር ደመወዙ 125 ብር እንዲቆረጥ የተደረገውን ኢ-ፍትሓዊ አሰራር መላው የሰራዊቱ አባላት  መቃወማቸውንና ብሶታቸውን እየገለፁ መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ አስታውቋል።