Tuesday, November 17, 2015

በሃገር አቀፍ ደረጃ የፍትህ አካላት የተሳተፍበት ሃገራዊ ስብሰባ በውቅሮ ከተማ በተካየደበት ጊዜ የትግራይ ክልል ህዝብ ከሁሉም በላይ ፍትህ አጥቶ እንደሚገኝ



በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ውቅሮ ከተማ በአገር ደረጃ ያሎው የፍትህ አፈፃፀም ሂደት የሚገምግም ስብሰባ ጥቅምት 19 /2008 ዓ/ም አገራዊ ስብሰባ በተካየደበት ጊዜ በትግራይ ክልል የፍትህ ሂደት የከፋ እንደሆነና የሚካየድበት በገንዘብና በዘመድ አዝማድ እንደሚፈፀም የገለፀው መረጃው በመሆኑም ለእድገት ዋና እንቅፋት ሆኖ ሱር ሰዶ ስለሚገኝ በቀላል መቅረፍ  እንደማይቻል በስብሰባው የተገኙት እንደገመገሙት ከቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን በላኩት መርጃ ለመረዳት ተችሏል።
        መርጃው ጨምሮ በትግራይ ክልል ገንዘብ የሌለው ድሃውን ህብረተሰብ በሕግ ፊት ቀርቦ አሸንፎ ለመውጣት የሚችሎው አጋጣሚ እንደሌለና እንዲሁም ትግራይ ክልል ከሌሎች ክልሎች የሚፈፀም የከፋ የፍትህ አሰጣጥ እንደሆነ ገምግሞ በተለይም ደግሞ ከሌሎች ክልሎች የመጡ ዳኞች የትግራይ ህዝብ በትጥቅ ትግል ያሳለፈው የከፋ ስቃይና መከራ ለፍትህና ለእኩልነት ብሎ ቡዙ መስዋእነትነትን ከፍሎ ከሌሎች በከፋ መልኩ ፍትህ ማጣቱ በጣም ያሳዝናል ብለው ሃሳባቸው እንደገለፁ ታውቛል።