Tuesday, November 17, 2015

በትግራይ ክልል የሚገኙ ትላልቅ ሆቴሎችና ቁርስ ቤቶች በስኳር መጥፋት ምክንያት ስራቸውን ለማቛረጥ እየተገደዱ መሆናቸው ታወቀ።



በመረጃው መሰረት በትግራይ ክልል የሚገኙ ትላልቅ ሆቴሎችና ቁርስ ቤቶች ስኳር እየተጠቀሙ የተለያዩ ምግቦችና መጠጦች በማዘጋጀት ወደ ተጠቃሚው ህብረተሰብ የሚያቀርቡ የነግድ ቤቶች የስኳር ከገበያ ጠቅልሎ በመጥፋቱ የተነሳ ነጋዴዎቹ ስራ እያቆሙ መሆኑን የገለፀው መረጃው በዚህም ምክንያት የእዚህ ተቋማት ባለቤቶች ከባድ የሆነ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ተገለፀ።
     መረጃው ጨምሮ እንደጠቆመው አልፎ አልፎም የተወሰነ ስኳር ቢመጣም በአካባቢው የሚኖሩ ባለ ስልጣናት  የስኳር አከፋፋይ የሚሆኑት ሰዎች ራሳቸው የመረጡዋቸው ግለ ሰዎች እያደሉ ቢገኙም  ለህብረተሰቡ እኩል እያከፋፈልነን በማለት ሊያደናግሩ ቢሞክሩም  የተቋማቱ ባለቤቶች ግን ምንም ሳንሰራ ግብር ክፈሉ እያላችሁ ከምታስገድዱን ለምን ሰኳር አታመጡልንም በማለት ለሚመለከታቸው  አካላት  ያቀረቡት ማመልከቻ ውጤት ስለሌለው  ለበላይ የመንግስት አመራሮች ምሬታቸውን እያሰሙ እንዴሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።