Friday, August 5, 2016

የሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዚህ ክረምት ወቅት ፀረ ትንኝ ዛንዜራ እንዲያገኙ ባለመቻላቸው የወባ በሽታ በከፍተኛ ደረጃ ሊተላለፍ እንደሚችል ስጋታቸው እየገለፁ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።



   ባገኘነው መረጃ መሰረት የሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዚህ ወቕት ፀረ ትንኝ ዛንዜራ በወቅቱ አልተሰጠንም ሲሉ የገለፁ ቢሆኑም የትግራይ ክልል የጤና ጉዳይ ለዚህ ወቅታዊ ጉዳይ ችላ ብሎ ቆይቷል ቆይቶ ደግሞ ከአሁን በፊት አገልግሎ የነበረ የተወሰነ የተቀደደ አረጌ ዛንዜራ የታደለ ቢሆንም በዚህ ደግሞ የወባ በሽታ በከፍተኛ ደረጃ ሊተላለፍ እንደሚችል የከተማው ነዋሪዎች ስጋታቸው በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ታዉቀዋል።
   የሰቲት አሁመራ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁት እየዘነበ ባለው ሃይለኛ ዝናብ ምክንያት አከባቢው ከፍተኛ አረንቓ የፈጠረ በመሆኑ መንግስት ደግሞ በአጭር ወቕት የዛንዜራ እርዳታ ካላደረገልን የወባ በሽታ በከባድ ሁኔታ ሊተላለፍ እንደሚችል አስገንዝበዋል
የሰቲት ሁመራ ከተማ የጤና ጥበቃ በበኩሉ የወባ በሽታ ለመከላከል ከፍተኛ እርብርብ እያካሄድኩ ነኝ ብሎ የሚገልፅ ቢሆንም ከወሬ ኣልፎ ግን በሰቲት ሑመራ ከተማ እስካሁን ድረስ የወባ በሽታ ለመከላከል የሆነ ይሁን ጥረት አለማካሄዱን ለማወቕ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment